ስለ እኔ

ተስፋዬ ተክሌ እባላለሁ በዚህች ታላቅ ከተማ በአዲስ አበባ የምርጫ ክልል 16 (በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9) የኢዜማ የፓርላማ እጩ ተወካይ ነኝ። ትውልዴ እና እድገቴ በዚሁ በአዲስ አበባ ሲሆን። ጉለሌ በሚገኘው መድኃኔ ዓለም ትምህርት ቤት ከአንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ተምሬ፣ በመቀጠል በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መካኒካል ኢንጂነሪንግ በመማር የባችልር ዲግሪዬን ተቀብያለሁ። ለትምህርት ዩንቨርሲቲ በነበርኩበት ወቅት የተለያዩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በንቃት እሳተፍ ነበር።

ባሁኑ ወቅት ለብዙ ዓመታት በሶፍትዌር ምህንድስና ሞያ ላይ ተሰማርቼ እየሰራሁ እገኛለሁ። ነዋሪነቴም ከባለቤቴና ልጆቼ ጋር በዚሁ በምንወዳት የአዲስ አበባ ከተማ ነው።

በፖለቲካ ተሳትፎዬ ሁሌም የኢትዮጵያዊነትን እሴት የሚያበረታቱ እና ከመርዛማ የጎሳ ፖለቲካ ይልቅ የዜግነትን ፖለቲካ የሚያስቀድሙትን የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ ቆይቻለሁ፣። በ1997 ዓ.ም. ቅንጅትን ለመምረጥ ወደ መርጫ ጣቢያ መሄዴ ከእኔን ካስደሰቱኝ ጊዜዎች አንዱ ነበር። ያ ቀን በትንሹ ያሳየን ትክክለኛ እና ጤናማ የፖለቲካ አካሄድ ምን አንደሚመስል ነበር።